West Arsi Zone Nensebo Woreda F/E/D/Bureau
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት አመት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ምርጥ ምድጃ (ማገዶ ቆጣቢ )
በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው::
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው ንግድ ፍቃድና በህጉ መሰረት ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ።
- የአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት)የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት በምን ዓይነተ ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15)ተከታታይ የስራ ቀናት እና በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ )ብር በነንሰቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸው ላይ በመ/ቤታችን በተሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለጽ በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 8 ለዚህ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ናሙና መታየት የሚገባውን ዕቃዎች በናሙናና በፎቶግራፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚቀርቡት ዕቃ ጥራት የጠበቀና በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት ኦርጅናል ዕቃ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ጥራቱ ያልተጠበቀና ኦርጅናል ያልሆነ ዕቃ ካቀረበ መመለስና መቀየር ግዴታ ይኖርበታል።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የተጠየቀው እቃዎች ሞዴል በተጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተሞልቶ ካልቀረበና ማንኛውም ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የድርጅቱ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የ20000 (ሃያ ሺህ) በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም ጥሬ ብር በነንሰቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ አለበት።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ15ኛው ቀን በ19/5/2017 በሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው የሥራ ቀን 20/5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 8 ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዢ ይሆናሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች መ/ቤቱ በሚሰጠው የአቅርቦት ትዕዛዝ መሠረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ እና በመ/ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 06 837 718፣ 09 13 265 326፣ 09 39 606 274ና 09 17 514 081 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት