በቀላሉ እንደዚህ ልግለፀው!
ድሮ ድሮ ጨረታ በአዋጅ ነበር የሚነገረው
…… ከዛ ጋዜጣ መጣ
…….ከዛ ዌብሳይት መጣ
…….ከዛ የኛ ሶፍትዌር
ይህንን ሶፍትዌር ለመስራት ከ1 አመት በላይ ተጠበንበታል። ለምን???
ድሮ ድሮ የሶፍትዌር ጨረታ ለመከታተል የተለያዩ ዌብሳይቶች ተመዝግቤ ነበረ
ምስራቅ አካባቢ የሚወጡ የሶፍትዌር ጨረታዎችን ብቻ ነበር መከታተል የምፈልገው
ግን ደሞ አንድ ወይም ሁለት ክልል ብቻ መርጦ መከታተል አይቻልም
ስለዚህ ኢትዮጵያ ላይ የሚወጡ የሶፍትዌር ጨረታዎች ሲላክልኝና የማይመለክተኝ ጨረታ በዝቶብኝ እና የሚመለከተኝ ጨረታ ሲያመልጠኝ ይህንን ሶፍትዌር ለመስራት ወሰንኩ።
ለምሳሌ ‘ዘይት’ ለመከታተል ምግብ ነክ ዘርፍ በሙሉ ይዘንብብሃል!
በዛ ላይ የማሸነፍ እድሌ ይሰፋል በሚል የተደገሙትን ጨረታዎች ብቻ መንጥሬ መከታተል እፈልግ ነበር ……
ለዛም ነው ይህን ማደን ራስ ምታት እንደሆነ ስለማውቅና አማራጮች ውስን በመሆናቸው ነው ይሄን ዌብሳይት ለመሰሎቼ ለማበርከት የወሰንኩት