ድሮ ድሮ የሶፍትዌር ጨረታ ለመከታተል የተለያዩ ዌብሳይቶች ተመዝግቤ ነበር
ለጓደኛዬ ደሞ ‘ቀለም’ እከታተልለት ነበር
ግን የማይመለክተኝ ጨረታ ሲሞላብኝ እና የሚመለከተኝ ጨረታ ሲያመልጠኝ ይህንን ሶፍትዌር ለመስራት ወሰንኩ።
ለምሳሌ ‘ቀለም’ ለመከታተል የህንፃ መሳሪያ ጨረታዎች በሙሉ ይዘንብብኛል! ከሲሚንቶ እስከ ጂፕሰም
በዛ ላይ የተደገሙትን ጨረታዎች ብቻ ነው መከታተል የምፈልገው ……የማሸነፍ እድሌ ስለሚሰፋ
ለዛም ነው እንደዚህ አይነት ጨረታ ማደን ራስ ምታት እንደሆነ ስለማውቅና አማራጮች ስለሌሉ ነው ይሄን ዌብሳይት ለመሰሎቼ ለማበርከት የወሰንኩት
መረጃ ለስኬትህ ምንጭ ነው! ግን እስከዛሬ መረጃ ለማግኘት ቀላል አልነበረም
አሁን ግን ሃሪፍ መላ እንዳበጀን ስንነራቹህ በደስታ ነው