Addis Zemen (Apr 14, 2025)
ሀገራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት እና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማለትም ለአስር ህንጻ ግንባታ እና ለት/መንገድ ልማት ጽ/ቤት መንገድ ስራ እና በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የተለያዩ ማቴሪያሎዎችን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
- ለወረዳው አስ/ር ጽ/ቤት ግንባታ የሚውል፡- አሸዋ፣ ጠጠር፣ የፍልጥ ድንጋይ እና ብሎኬት ግዥ፣
- የህንጻ መሣሪያዎች እና የቧንቧ ዕቃዎች
- ዘመናዊ የንብ ቀፎ
- የደን ችግኝ ዘር እና የምግብ ምርጥ ዘር
- የመንገድ ከፈታ አፈር ሥራ የዶዘር ማሽነሪ ኪራይ/መኮናተር
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ተሻሽሎ በወጣው በመንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 ዓ/ም መሰረት፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/ያላቸው፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን መረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከሽያጭ ዋጋ ላይ ለመንግሥት ግብር 2% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ፤
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዕቃ አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ሁኔታ በአይተም ወይም በጥቅል ሊሆን ይችላል፤
- የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለዶዘር ማሸን ከመንግሥት መ/ቤት የመልካም የስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፤ ተጫራቹ የግል ሊብሬ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፤
- የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት ኦርጂናሉን በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በቁጫ አልፋ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ-5 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታ ሂደቱ ላይ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% የማስያዝ ግዴታ አለበት፤
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ቀጫ አልፋ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-5 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በጥሬ ወይም የኢትዮ ባንከ ቼክ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ህጋዊ CPO ለሚሳተፉበት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- የጨረታ ሣጥኑ የሚታሸገው የጨረታ ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ አውራጅና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ወይም የጨረታ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡-
- የደን ችግኝ ዘር እና የምግብ ምርጥ ዘር ግዥ ጨረታ ተወዳዳሪዎች ከቫት ነጻ የሆኑበትን የድጋፍ ደብዳቤ መረጃ አያይዞ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ለዶዘር ማሽነሪ ኪራይ ሞዴል ከ2010 ወዲህ ስሪት CAT D8R በአሁኑ ገበያ ያለ መሆን አለበት። ለዶዘር ማሽን የጭነት ዋጋ በአከራዩ የሚሸፈን ይሆናል።
- የዶዘር ማሽን አሸናፊ ተጫራች በውድድሩ ካሸነፉ በሰባት ቀናት ውስጥ ለአሰሪው መ/ቤት ማሽኑን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃው ከጥራትና ደረጃ ዝቅ ቢል፣ ዕቃው ቢጎድል ከተዋወለው ከውሉ ጊዜው ቢያልፍ በሕግ መሰረት ለመንግስት ከገባው ከጠቅላላ ውል ገንዘብ ላይ 20% የሚደርሰውን ብር ተቀጥቶ ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ በፍ/ህ/ቁጥር 2005 መሰረት የፀና ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለበለ መረጃ ስልክ፡- 09 16 66 99 82/ 09 26 36 60 87/ 09 76 13 56 48/ 09 84 66 61 89 ደውለው ይጠይቁ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የቁጫ ወ/ፋ/ጽ/ቤት