Addis Zemen (Mar 21, 2025)

ግልጽና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ //ቤት የጉምሩከ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት 19/07/2017 . በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት እና ከአዋሽ ጉምሩክ //ቤት ማየት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች፡

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫረቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 19/7/2017 . እስከ ጠዋቱ 345 እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 500 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ //ቤት በእካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።

3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሠርተው በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋ።

4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ///ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

.

የጨረታ ቦታ

 የጨረታው ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አዋሽ ///ቤት

ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ

ጫማዎች አልባሳት ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ መነፅር፣ ምግብ ነክ ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልጽ ጨረታ 19/07/2017 እስከ ጠዋቱ 345 ለሐራጅ ጨረታ እስከ 445

ለግልጽ ጨረታ 19/07/2017 እስከ ጠዋቱ 400 ለሐራጅ ጨረታ 500 ሰዓት

5. የጨረታው መክፈቻ ቦታበቃሊቲ ///ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል

6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ 3 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል።

8. ከላይ በተ. 7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9. /ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 224 1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ጉምሩክ //ቤት