Addis Zemen (Mar 21, 2025)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ
ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር GGWW/0027/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው ከአረዳ እስከ ጅማ ድረስ ያለው የመንገድ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/RC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች።
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ብር 100000 (መቶ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ተከታታይ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
ማሳሰቢያ:-
- በአፈፃፀም ምከንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
- በወረዳው ውስጥ ሁለትና ከዚያ በላይ ፕሮጀክት ይዞ ስራውን ያልጨረሰ ተጫራች መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልክታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ሳይወስድ /ሳይጠይቅ ስራ መጀመር የሚችል።
ለበለጠ መረጃ የገ/ጉ/ወ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
ስልክ ቁጥር፡- 0113360162/146 ይደውሉ
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት