Addis Zemen (Mar 21, 2025)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር የሥልጠና ግብዓቶችን ግዥ፤ የመጽሐፍ ግዥ፤ የደንብ ልብስ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተ/ቁ
| የዕቃው ዓይነት
| የጨረታ ማስከበሪያ መጠን | ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
ሎት1 | የኤሌክትሪክ ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20,000 | ሎት 10 | የቆዳ /ሌዘር/ ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20,000 |
ሎት2 | ጠቅላላ የብረታ ብረት ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20,000 | ሎት11 | የሰርቨይንግና ድራፍቲንግ ዲፓርትመንት ዕቃ | 10,000 |
ሎት3 | የአውቶሞቲቪ ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20,000 | ሎት12 | የከተማ ግብርና ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 10,000
|
ሎት4 | የእንጨት ሥራ ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20,000 | ሎት13 | አላቂ የጽህፈት መሣሪያ | 10,000 |
ሎት5 | የአይሲቲ ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20,000
| ሎት14 | አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
| 10,000
|
ሎት6 | የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20,000
| ሎት15 | የደንብ ልብስ
| 10,000
|
ሎት7 | የሆቴልና ቱሪዝም ዲፓርመንት ዕቃዎች | 20,000
| ሎት16 | ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
| 10,000
|
ሎት8 | የፀጉር ሥራ ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20.000
| ሎት17 | የንባብ መጽሐፍ ግዥ
| 2,000
|
ሎት9 | የጋርመንት ዲፓርትመንት ዕቃዎች | 20,000
|
|
|
|
ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት አለባቸው፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው።
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከመንግሥት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ CPO ውን ቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በመክተት በደንብ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ኤንቨሎፑ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ መገለፅ ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለተጫረቱበት ዕቃዎች ትክክለኛውን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በ4፡30 ጨረታው ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- በጨረታው ተሣታፊ የሚሆነው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011- 4173226/011-8-495158/011-4-343336/ 01114173226/
የመ/ቤቱ ስድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደብረ ዘይት መንገድ መውጫ ፍተሻ ሳይደርስ የሺ ቶታል አለፍ ብሎ ወደ ግራ በሚወስደው መንገድ 800 ሜትር ገባ ብሎ ነው።
የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ