Reporter (Mar 19, 2025)

ያገ ንብረቶችን መሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን፡-

  1. የህክምና መገልገያ እቃዎች
  2.  አልጋዎች እና ኮቾች
  3. መኪኖች ባሉበት ሁኔታ
  4. የፕላስቲክ እና የእንጨት ወንበሮች እንዲሁም ሶፋዎች
  5.  ጄኔሬተሮች
  6. የላውንደሪ ማጠቢያ ማሽኖች
  7. የሽንት ቤት መቀመጫዎች
  8. ብረቶች እና ቁርጥራጭ ላሜራዎች ፣ እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የሆስፒታል ያገለገሉ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤

በዚህም መሰረት ፡-

  1. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከገንዘብ ተቀባይ ክፍል ከደረሰኝ ጋር በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
  2.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚጫረቱትን ጠቅላላ ዋጋ 20% በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የዋስትና ሰነድ ከሚሰጡት ዋጋ ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ንብረቱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ሲኤምሲ ከሚገኘው ግምጃ ቤት ፣ቦሌ ሸዋ ዳቦ ከሚገኘው ቤተዛታ ክሊኒክ እንዲሁም እስታዲየም በሚገኘው በቤተዛታ ሆስፒታል በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ኦርጅናል ማህተም ካለበት የጨረታ ሰነድ እና ደረሰኝ ጋር አባሪ በማድረግ ከመጋቢት 29, 2017 እስከ ሚያዝያ 1, 2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ድረስ እስታዲየም በሚገኘው በቤተዛታ ሆስፒታል በፋሲሊቲ ዋና ክፍል በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ጨረታው የሚከፈተው ሚያዝያ 2, 2017 ዓ.ም እስታዲየም በሚገኘው በቤተዛታ ሆስፒታል አዲሱ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በስብሰባ ክፍል ከቀኑ 5 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።

ማሳሰቢያ – ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

011-553-5980  እና 0913-674-518