Addis Zemen (Mar 07, 2025)
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 በፋብሪካ የተመረተ (ኢንዱስትሪያል ጋቢዮን)፣
- ሎት 2 የወንዝ ድንጋይና ጥቁር የግንብ ድንጋይ፣
- ሎት 3 ኤክስካቫተር ባለ ቼይን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. የጨረታ መለያ ቁጥር፡– ቃ/ወ/ግ/ጨ/004/2017
2. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ቲን ነምበር ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና መረጃ ኦሪጅናል እና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ ሲኖርበት የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. የሚፈለገውን የእቃውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሠነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 – 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 – 45,000 (አርባ አምስት ሺህ ብር) ለሎት 3 – 35,000 (ሠላሳ አምስት ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድ ቦንድ ከሆነ ከ60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ በየሎቱ 10% ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ስምና አድራሻውን በመጻፍ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ፖስታውን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ እለት በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው እለት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
7. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ጋቢዮትን ቃሉ ወረዳ ግብርና ንብረት ክፍል፣ የወንዝ ድንጋይና ጥቁር የግንብ ድንጋይ እንዲሁም ኤክስካቫተር ኪራይ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተጠቀሠው ቀበሌዎች ለማቅረብ በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡
9. ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
10. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ካሸነፈው አቅርቦት ወይም አገልግሎት ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉቸው ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቃሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁ 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 551-47 56 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን