Addis Zemen (Mar 07, 2025)

2 ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2017

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቦሌ /ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር //ቤት

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፤
  • ሎት 3 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፤
  • ሎት 4 ቋሚ ዕቃዎች፤
  • ሎት 5 የፕሪንተር ቀለም፣
  • ሎት 6 የመኪና ዕቃዎች፣
  • ሎት 7 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 8 የሆቴል መስተንግዶ፣
  • ሎት 9 የቲተርና ህትመት፣
  • ሎት 10 የኮምፒውተር፣ ስካነር ፕሪንተር እና ሌሎች የቢሮ ጥገና፣
  • ሎት 11 የመኪና ኪራይ፣
  • ሎት 12 ኤምዴፍ ፈርኒቸር በካሬ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በመስኩ ለተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፤

1. ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፍላሽ 64 32 GB ማስታወሻ ደብተር፣ ክላሰር 250 ግራም፣ ሸራ ፕላስተር የመሳሰሉት፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች ኤርፍሬሽነር፤ ፍሊት፤ አልኮል፤ ሳኒታይዘር፤ በረኪና፤ ፎጣ የመሳሰሉት፣ ሎት 3 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች የኤሌትሪክ ማከፋፈያ ባለ 3 ቀዳዳ፤ መቀስ ትንሹ፤ መቀስ ትልቁ፤ ሳይንትፊክ ካልኩሌተር የወረቀት ትሪ ባለ 3 ተደራራቢ የመሳሰሉት፤ ሎት 4 ቋሚ ዕቃዎች ስካነር፤ መጠረዣ ማሽን፤ ታብሌት ኮምፒውተር፤ እስታብላይዘር 1500 ዋት ግዥ፣ ሎት 5 የፕሪንተር ቀለም፣ ሎት 6 የመኪና ዕቃዎችና ጌጣጌጥ ክሪክ፤ የመኪና ልብስ፤ የመኪና ሽታ፤ የመሳሰሉት፣ ሎት 7 የደንብ ልብስ የወንድና የሴት ጫማና የውስጥ ልብስ ጨርቅ፣ ሎት 8 የሆቴል መስተንግዶ፤ ሎት 9 ህትመትና ቲተር የስምና የስራ ድርሻ፣ ሎት 10 የኮምፒውተር ስካነር ፕሪንተር እና ሌሎች ጥገና፣ ሎት 11 የመኪና ኪራይ፣ ሎት 12 ኤምዴፍ ፈርኒቸርግዥ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር 2,000 ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች 2,000 ሎት 3 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች 2,000 ሎት 4 ቋሚ ዕቃዎች ግዥ 5,000 ሎት 5 የፕሪንተር ቀለም 5,000 ሎት 6 የመኪና ዕቃዎችና ጌጣጌጥ ብር 5,000 ሎት 7 የደንብ ልብስ ብር 1,000 ሎት 8 የሆቴል መስተንግዶ ብር 5,000 የቲተርና ህትመት ብር 2000 የኮምፒውተር ስካነር ፕሪንተር እና ሌሎች ጥገና 2000 ብር ሎት 11 የመኪና ኪራይ 2000 ብር ሎት 12 ኤምዴፍ ፈርኒቸር 2000 ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳያር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቦሌ /ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ /ቤት ስቕ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤

3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት 230 እስከ 1130 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብቻ በመክፈል ከቅ//ቤታችን የአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው በመግለጽ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ብቻ /ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤

5. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

6. ጨረታው 11ኛው ተከታታይ የስራ ቀን 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤

7. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን (የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናልና እና የተጠየቁ አስፈላጊ

የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፤

9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለው ማለት አይችልም፤

10. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፤

11. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል፤

12. ተጫራቾች ለምታቀርቧቸው ናሙናዎች የምታመጡበት ዕቃዎች ጠንካራ እና በቀላሉ ሊቀደዱ የማይችሉ መሆን አለባቸው

አድራሻ፡መገናኛ የቦሌ /ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ ምድር ላይ አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል

ለበለጠ መረጃ በስ..0913-54-1013 እና 0912-01–4919 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቦሌ /ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር //ቤት