Addis Zemen (Mar 07, 2025)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አጋር አራዳ ኃላ/የተ/ የሸማቾች የህብረት ስራ ዩኒየን የ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሂሳብ ኦዲት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡–
- ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችል የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
- ከኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን በሂሳብ ምርመራ የተደራጀ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦሪጅናል፤
- የጨረታ ማስረከቢያ ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ልክ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፐ ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ሰነድ ከድርጅቱ ጽ/ቤት 100 ብር በመግዛት የጨረታ ሰነዱን መሙላትና የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ፤
የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ፡–
በድርጅቱ ጽ/ቤት ሳንፎርድ ት/ቤት ወረዳ 7 አስተዳደር ጀርባ
ስልክ ቁጥር 09-20-72-96-94 /09-13-71-25-44
የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ ቀን፡– በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ 11/7/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ያበቃል።
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡– በ12/7/2017 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡–ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኑ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አጋር አራዳ ኃላ/የተ/ የሸማቾች የህብረት ስራ ዩኒየን