Sede Muja Woreda FEDB

በኩር
(Feb 03, 2025)

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎

በደ/ጎንደር ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግን/አስ ቡድን ለ2017 በጀት አመት ለመንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የዶዘር ማሽን ኪራይ በግልጽ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ፡-

  1. በየዘርፉ ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200‚000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ሙሉ አድራሻቸውን በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም መምታት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ 50 /አምሳ / ብር በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7.  የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ውን ካሸነፉ በኃላ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውላል፡፡
  11. ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይታሸጋል በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው በሚከፈትበት ቀን ቢገኙም ባይገኙም ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  12. ከጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
  13. ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  14. በማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. የመልካም ሥራ አፈጻጸም መገለጫ እና ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  17. ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ እዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  18. የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደርያ ሃሳብ ላይ ለወጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  19.  ስለጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስሥልክ ቁጥር 09 18 28 07 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት