
Addis Ababa City Roads Authority
አዲስ ዘመን
(Feb 05, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር ፡–አከመበ/ግብዓት/ቡ-2/026/2017
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2017 በጀት ዓመት
- የተለያዩ አይነት ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች እና
- ታብሌት ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የሚገዛው ዕቃ ዓይነት | መለኪያ | ብዛት | ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ | የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት | የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
1 | ዴስክቶፕ ኮምፒውተር Core i7 (Hligh-performance Type C desktop for advanced engineering design works) | በቁጥር | 30 | 60 ቀን
| የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት | የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት | 150,000.00 |
2 | ላፕቶፕ ኮምፒውተር Core i7 (High-performance Type-C Laptop for advanced engineering design works) | በቁጥር | 4 | 40,000.00 | |||
3 | ላፕቶፕ ኮምፒውተር Core i7 (Laptop for GIS Based Road Asset Data Collection & Management, and Social Media services) | በቁጥር | 10 | 100,000.00 | |||
4 | Editing computer (High-performance Desktop suitable for Graphics design and Advanced processing) | በቁጥር | 2 | 100,000 00 | |||
5 | Tablet (Tablet for GIS Based Road Asset Data Collection & Management, and Social Media services) | በቁጥር | 3 | 170,000.00 |
ስለዚህ፣
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ–ገፅ (WWW.PP.gov.et) መዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ተጨማሪ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ ከላይ እሰከተጠቀሰበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ከባለሥት መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ Certified payment (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ለእያንዳንዱ ዕቃ በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ሲሆን ለሁለቱም ሎት የሚወዳደር ከሆነ ግን ከ500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ መብለጥ የለበትም፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መከፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፤
ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳደደርስ
ስልክ ቁጥር፡– 011 372 2825/011 371 4103
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን