
Accessible Ethiopia
አዲስ ዘመን
(Feb 05, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
አክሴሰብል ኢትዮጵያ የተባለ በሁሉም የአካል ጉዳተኞች ላይ የሚሠራ ድርጅት ሲገለገልበት የነበረ ያገለገለ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፡–
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተሽከርካሪው በሚገኝበት ቦታ መገናኛ ስለሺ ሕንፃ 5ኛ ፎቆ ቢሮ ቁጥር 502/2 በመገኘቱ ከጠዋቱ 3፡oo እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሠርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት በጸደቀ በ 3 ( ሦስት ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ /ፖስታ/ በአዲስ አበባ ከተማ በድርጅቱ ቢሮ መገናኛ ስለሺ ህንፃ 5ኛ ፎቆ ቢሮ ቁጥር 502/2 በመገኘት የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው ፡፡ በሰባተኛው ቀን የጨረታ ሰነዱ የሚገባው እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒ.አ. ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪ ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ 500 /አምስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ ተከታታይ ቀናት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በሰባተኛው ቀን ሰነዱ የሚሸጠው እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ7ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት የተጫራቾቹ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው መገናኛ ስለሺ ሕንፃ 5ኛ ፎቆ ቢሮ ቁጥር 502/2 ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፣
- ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ወጪ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118686337/0911-00 6372/0912-28 29 03
አክሴሰብል ኢትዮጵያ