
Dembacha City Administration FEDB
በኩር
(Jan 27, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
በዘርፍ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ ቤት በደረሰኝ በመክፈል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ስለትክክለኛነቱ በማህተም በማረጋገጥ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደምበጫ ከተማ /ገ/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ/ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ዋጋውን በመሙላት፣ የጨረታ ሠነዱን ገልፆ በመፃፍ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎችን በአንድ ፖስታ በማድረግ በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም፣ ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ በማስቀመጥ ለደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በተራ ቁጥር 10 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሠነዱ ላይ ከተገለፀው የዕቃ ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ውጪ ሌላ መጥቀስ አይቻልም፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ደምበጫ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
- የግዥ አቅርቦቱን አሸናፊው ውል በያዘ አስር ቀናት ውስጥ ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት በማጓጓዝ እና በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ደምበጫ ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን በሎት በጥቅል ዋጋ በማወዳደር አሸናፊውን የሚለይ ይሆናል፡፡
- ግብርና ታክስ የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ቅድሚያ ክፍያ ጽ/ቤቱ የማይከፍል መሆኑ ይታወቅ፡፡
- ተጫራጮች የጨረታ ሰነዱን ሙሉ በሙሉ የመሙላት ግዴታ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 773 0281/092 051 4020/091 292 8346/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
ደምበጫ ከተማ ገንዘብ /ጽ/ቤት