
Ethiopian Broadcast Corporation
አዲስ ዘመን
(Jan 28, 2025)
ድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር NCB007/2017 እና NCB009/2017
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የግንባታ ዕቃዎች እና የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ትክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሸጎሌ በሚገኘው በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ መሠረት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁ | የግዥው ዓይነት
| የጨረታ መለያ ቁጥር | የጨረታው | ማስከበሪያ/በብር/ | የጨረታ መዝጊያ | የጨረታ መክፈቻ | ||
ቀን | ሰዓት | ቀን | ሰዓት | ||||
1 | የግንባታ ዕቃዎች ሎት 2 | NCB 007/2017
| 10,000.00
| በ16ኛው ቀን
| 5፡30 | በ16ኛው ቀን | 5:45
|
2 | የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት | NCB 009/2017
| 10,000.00
| በ16ኛው ቀን
| 8፡00 | በ16ኛው ቀን | 8:15
|
4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የመወዳደሪያ ሰነዶች ፋይናንሺያል አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በፖስታ ለየብቻው አሽገው የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጻፍ ማህተማቸውን በመምታት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ በሠንጠረዡ መሠረት በኮርፖሬሽኑ ግዥ ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸጎሌ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚያገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011-517-25-21 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን