
Addis Ababa Abattoirs Enterprise
ቱመርካቶ.ኮም
(Jan 28, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 7/2017
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
- የውሃ ፓምፕ/Water pump/፣ ሰብመርሰብል ፓምፕ/Submersible pump/፣ የሞራ መሳቢያ ፓምፕ፣ ሰርቦ ሞተር እና ጊር ፓምፕ፣
- የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣
- መካከለኛ እና ከባድ ተሽከርካሪ ግዥ፣
- የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ፣
- የበሬ ክብደት ማንሻ፣ የሸሆና ጥፍር መንቀያ እና የጎድን መሰንጠቂያ ማሽን፣
- የተለያዩ የቴክኒክ መገልገያ እቃዎች እና ሌሎች እቃዎች፣
- ለህንፃ ግንባታ እና ጥገና የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎች እና የህንፃ ቀለሞች፣
ማንኛውም ተጫራች፡-
- በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያጋግጥ የምስክር ወረቀት ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ.፣ በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ወይንም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል፣
- የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
- ጨረታው የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ11 4 66 47 05 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት