
Gamo Zone Finance Department
አዲስ ዘመን
(Jan 25, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት
- ሎት1) የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የቢሮ እድሳት
- ሎት2) የዞኑ ከተማና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ግንባታና ጥገና ስራ
- ሎት3) የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የፊት ለፊት አጥርና መግቢያ በር ግንባታ
- ሎት4) በዞኑ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ በጎጎራ ሰፈራ ጣቢያ የመሸጫ ሼድ ግንባታ
- ሎት5) በዞኑ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ በሀመሳ ሰፈራ ጣቢያ የመሸጫ ሼድ ግንባታ ስራ ደረጃቸው Bc/Gc 8 በተደራጁ ማህበራት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡–
1) የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለ2017 በጀት የንግድ ሥራ ፈቃድ ያሳደሱ ፣ በዞን እና ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ወይም በክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ እና የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት 2017 በጀት ዓመት ያሳደሱ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ ለአቅራቢነት የተመዘገቡ ሆነው ሰነድ ሲገዙ እና በጨረታ መክፈቻ ዕለት ኦርጅናል የህጋዊነት ሰነዳቸውን ለማመሳከሪያነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2) ማንኛውም ተጫራች አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችን ከራሳቸው አቅርበው መስራት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3) የጨረታ ማስከበሪያ (BlD Security) ሎት1) 15,000(አስራ አምስት ሺህ ብር) ሎት2) 95,000(ዘጠና አምስት ሺህ ብር) ሎት3) 35,000(ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) ሎት4) 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር) ሎት5) 55,000(ሃምሳ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) (በጥሬ ገንዘብ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት (unconditional BlD BOND) ማስያዣ በኦርጂናል የህጋዊነት ሰነድ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21(ሃያ አንደኛው) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ ብር) በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክን አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኝ በመቁረጥ ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው ደረሰኙን በማሳየት የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
5) ማንኛውም ተጫራቾች ከውድድሩ በፊት የሥራ ሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ የነጠላ ዋጋ መሙላት አለበት ፡፡
6) የፋይናንሻል ጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፍክ ኮፒው በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት ፣ በሶስቱም ፖስታዎች ላይ ስም ፣ አድራሻና የፕሮጀክቱ ስም በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም እንዲሁም የህጋዊነት ሰነዶችን አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ እና የጨረታ ማስበሪያ (BID Security) በተለያዬ ፖስታ ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሁኔታ ታሽጎ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን በታሸገ በአንድ እናት ፖስታ እላዩ ላይ ማህተም ፣ አድራሻና ስም ጽፎ በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 22ተኛ(ሃያ ሁለተኛው) ቀን 4፡00 ድረስ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7) ጨረታው በ22ተኛ(ሃያ ሁለተኛው) ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-881-3338 ጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መደወል ይቻላል፡፡
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
አርባ ምንጭ