
Shemelese Habte Secondary School
አዲስ ዘመን
(Jan 25, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር፡-02/2017
የሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተገለፁትን
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች ፣
- ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 3 የደንብ ልብሶች፣
- ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች
- ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 6 የተማሪዎች አጋዥ መፅሐፍት፣
- ሎት 7 የትምህርት መርጃ ዕቃዎች (የማዕከል)፣
- ሎት 8 የህክምና ዕቃዎች፣
- 9 የሠራተኞች የመታወቂያ ሕትመት ሥራ በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች፡-
- በተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃዎችን ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የዕቃ ዓይነቶች በተናጠል የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ብር 8000 (ስምንት ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ ሲሆን CPO ኦርጅናል ሰነድ የታሸገበት ኤንቨሎፕ ውስጥ መካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዕቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው በተጠቀሰው መጠየቂያ መሠረት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ በት/ቤቱ ሂሣብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 /አንድ/ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጥበትን ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ በመሙላት እና ሌሎች ማስረጃዎችን በማህተም በማረጋገጥ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10 የስራ ቀን ቀን 11፡30 ሰዓት በታሸገው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ከ7ኛው ከሰባተኛው ቀን ቀጥሎ ውል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ አለበት፣
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡ አድራሻ ፡- ገነት ሆቴል ጀርባ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት