
Oromia Forest and Wild Life Enterprise Harerge Branch
አዲስ ዘመን
(Jan 25, 2025)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
የአሮጌ ብረታብረት ሽያጭ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር OFWEDH/MM-01/2017
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ ድንድን ድስትሪክት ላይ የሚገኘውን አሮጌ ብረታብረትና ሌሎች ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም:-
- የብረታብረት እና ተዛማጅ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የቫት(VAT) ተመዝጋቢ የሆነ የንግድ መለያ ቁጥር (TIN number) ያለው ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታው መወዳደር ይችላል። ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጭሮ ከተማ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ውሃ ልማት ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ ቢሮ ቁጥር 2 ወይም ቀበና ሼል ኦይል ሊቢያ/ አጠገብ ከሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የሚሆን ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ለምትጫረቱ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች፣ በድርጅቱ ሐረርጌ ቅርንጫፍ ለምትጫረቱ ጭሮ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በተረጋገጠ ደረሰኝ(CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ባሉበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 2555 12239 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ