
Gode Kindergarten & Elementary School
አዲስ ዘመን
(Jan 24, 2025)
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የጎዴ ቅድመ አንደኛ ና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ሎት 01 እስከ ሎት 05 ድረስ ያሉት ዕቃዎች፡–
- የደንብ ልብስ
- የጽዳት እቃዎች
- አላቂ ትምህርት እቃዎች
- ለአገልግሎት
- ለጭነት
በጨረታው ለመወዳደር ለምትፈልጉ
- ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ።
- በገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው እቃና አገልግሎት ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡
- ተጫራቹ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን ዓይነት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ በተከታታይ አስር የስራ ቀን በስራ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የጎዴ ቅድመ አንደኛ ና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበት በሲ.ፒ.ኦ. ብር የአንድ ሎት 10,000 /አስር ሺህ ብር/ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገባ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ እስከነቫቱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፐ ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ክፍት ነው፡፡ በ11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት 11፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊዎች በጨረታው አሸናፊነት ከተገለፀው ቀን ከ7ኛው ቀን በኋላ መልካም አስተሳሰብ ዋስትና 10 ፐርሰት በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል በመፈፀም ያሸነፉበትን እቃ ማቅረብ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
- እያንዳንዱ ተጫራች የሚያስጋባቸውን እቃዎች ሳምፕል ሲያመጡ በፎቶ የሚያስፈልጉትን እቃዎች ማምጣት ይኖርበታል።
አድራሻ ፡– የካ አባዶ ወረዳ 14 ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ /011 866 8072/
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ት/ት መምሪያ