Worabe Comprehensive Specialized Hospital
አዲስ ዘመን
(Jan 04, 2025)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 በጀት ዓመት በሆስፒታሉ ፍሳሽ የማስወገድ አገልግሎት የሚሰጥ መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለስራው የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዳቸው በመክፈል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ተፈላጊ ስራውን መስራት የሚያስችላቸውን በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የታደሰ ሊብሬ፣ የተመረተበት ጊዜ 1990 ከዚያ በላይና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 10,000/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ CPO /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ08፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኃላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 329 9270 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ
ሆስፒታል