![Awash Custom Commission Branch Office](https://diretenders.com/wp-content/plugins/wp-job-manager/assets/images/company.png)
Awash Custom Commission Branch Office
አዲስ ዘመን
(Jan 04, 2025)
የግልጽና ሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ 02/05/2017 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በመግዛትና ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት ከታች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ መስፈርቶች፡-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለoመሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር እያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 02/05/17 ዓ.ም እስከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከረፋዱ 5:00 ሰዓት የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታውን ሰነድ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገቢ አሰባሰብ ቢሮ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በአዋሽ ጉ ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
- ለጨረታ በቀረበ ተሽከርካሪ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ እና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተ.ቁ |
የጨረታ ቦታ
|
የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች
|
የዕቃዎች መመልከቻ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ ቀን እና የመፈቻ ቀንና |
1 |
አዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ ቤት
|
በግልጽ ጨረታና በሐራጅ
|
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የስፖርት እቃዎች፣ አርቴፊሻል ጌጣ ጌጦች፣ የሞባይል ቀፎ፣ አልሙኒየም ፕሮፋይል፣ ሴራሚክ፣ ምግብ ነክ፣ ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች እና ተሽከርካሪ |
ለግልጽ ጨረታ በ02/05/2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ለሐራጅ ጨረታ እስከ 4፡45 ሰዓት
|
ለግልጽ ጨረታ በ02/05/2017 ዓ.ም እስከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ለሐራጅ ጨረታ 5፡00 ሰዓት
|
6. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በአዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0222-24 14 02 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር 13/2017 ለጨረታ የቀረበ የተሽከርካሪ መረጃ
ተ.ቁ |
የተሸከርካሪ አይነት
|
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
ሞዴል |
የስሪት ሀገር
|
የምርት ዘመን |
የፈረስ ጉልበት (cc) |
1 |
TOYOTA CARINA
|
SB153ABKOOL008417
|
– |
AT1902- BEMNKW |
JAPAN |
1995
|
1600
|
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት