
የቦንጋ እፅዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል
አዲስ ዘመን
(Jan 02, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 0.1/2017
የቦንጋ እጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል በ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ ደንብ ልብስና የደብል ካፕ ፎርድ መኪና ጎማ እንዲሁም ለላብራቶሪ አገልግሎት የሚውል የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀምና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
- 1. ሎት –01 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ
- 2. ሎት– 02 የደንብ ልብስ ግዥ
- 3. ሎት– 03 የደብል ካፒ ፎርድ መኪና ጎማ ግዥ
- 4. ሎት– 04 የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና
በዚሁ መሠረት፡–
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- ሕጋዊ የኮንስትራክሽን የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ እዲሁም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት ሰርቲፍኬት (TIN NO) ያላቸው
- በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበርያ ለሎት-01 ብር 4,000.00 እና ለሎት-03 ብር 5,000.00 ለሎት-04 10,000 በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የምትችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 01 ለሎት 02 ለሎት 03 ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እንዲሁም ለሎት 04 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር ብቻ/በማዕከሉ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000099955361 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነድ ከማዕከሉ ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የግዥን እንዲሁም ለ21 ቀናት የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገናን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን ዋናና ኮፒ ለየብቻ ተፈላጊ መረጃዎች ጋር በፖስታ በማሸግ በቦንጋ እፅ/ዘር/ጥ/ቁ/ም/ በማዕከል የግዥና ክፍያ ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ሲመልሱ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ ላይ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡
- ጨረታው ለግዥዎች በ16ኛ ቀን ለውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና በ22 ቀን ከሰዓት 08፡30 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ 09፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል የተጠቀሰው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማብራሪያ መጠየቅ የሚችለው ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ(10) ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
- ውጤት አስመልክቶ ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለሰባት/ 07/ ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው፡፡
- የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና ተጫራቾች አሸናፊው ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /Performance bond/ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡ ዕቃ ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርቦ ውል በመግባት የሚያቀርባቸው ዕቃዎች እስከ ማዕከሉ ግቢ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በውሉ መሰረት ዕቃዎች ባይቀርቡ ስራው ቢስተጓጎል በግዥ ኤጀንሲ ደንብ ወይንም በኮንስትራክሽን ህግ መሰረት ውል ተቀባይ እንዲጠየቅ ይደረጋል::
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ነገርግን በእያንዳንዱ ሎት ላይ የተካተቱ ሀሳቦች በጋዜጣ እንደወጣ ይቆጠራል፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0917 476 163 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የቦንጋ እፅ/ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል