Bench Maji Zone Sheko Zone Finance Economic Development Command
አዲስ ዘመን
(Dec 30, 2024)
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት
- በጊዲ ቤንች ወረዳ የሻይ ቀበሌ IPD Block ግንባታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በግንባታ ዘርፍ BC/GC -5(አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ከሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በማለት ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ፋይናንሻል እና ቴከኒካል አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱ ለየብቻ በማሸግ እና በጥቅል በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ መቅረብ አለበት፤
- ተጫራቾች እያንዳንዱን በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦሪጅናል እና ኮፒ የሚል ጽሑፍ ተጽፎበት፣ ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው በወጣ 21ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡– ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የማይመለስ ኮፒ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 135 5629
በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/ መምሪያ
ሚዛን አማን