Ethiopian Heritage Trust (EHT)
ሪፖርተር
(Dec 29, 2024)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር (ኢቅባማ)
የጨረታ ቁጥር ኢቅባማ/ግጨ-01/2017
የቁም ባሕር ዛፍ ሽያጭ ግልጽ ጨረታ
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለደራ ማሕበር ከሚያስተዳድራቸው በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ውስጥ በሚገኙ ሁለት (2) የተለያዩ ቦታዎች ጠቅላላ ስፋቱ 45.24 ሄክታር ላይ ያረፉ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የቁም ባህር ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ይህ ለተለያየ አገልግሎት የሚውል የቁም ባህር ዛፎች በሁለት ክፍልፋይ/ Cepartment/ የተከፋፈሉ ሲሆን፣ ክፍልዮቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡
ተ.ቁ |
የቁም ባህርዛፉ ክፍልፋይ / Cepartment/ |
መለኪያ |
የቁም ባህር ዛፉ የያዘው የመሬት ስፋት በሄክታር |
አጠቃላይ የባህር ዛፍ መጠን (በሚትር ኩብ) |
1 |
ፈረንሳይ (F1) |
በጥቅል |
20.47 |
2405.79 |
2 |
አክመል (AK2) |
በጥቅል |
24.77 |
2525.28 |
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3፡00-6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡00 ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን የዛፍ ክፍልፋይ /Compartment/ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ሥም በማዘጋጀት ከቸረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በተጠየቀው መሠረት ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የማፈለጉትን የአያንዳንዱን የዛፍ ክፍልፋይ /Compartment/ የመግዣ ዋጋ በተያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ብቻ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት በሰም በታሸገ ኤንቨሎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ከታች በተለገጸው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- አሸናፊ ተጫራች (ቾች) የጨረታ ወጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከማሕበሩ ጋር ውል መፈራረም አለበት/አለባቸው/ ክፍያው ከተፈጸመ ጀምሮ ለእያንዳንዱ ክፍልፋይ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ባህዛፉን ማንሳት አለበት አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይውል እና በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ቅርስ ባለደራ ማሕበር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚከተሉትን ሰነዶች የማቅረብ ገዴታ አለባቸው። ከተፈለገው ሥራ ጋር ተዛማጅነት ያለው እና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች/ቾች/ አሸናፊነቱ /ታቸው/ ተገልጾለት /ላቸው/ ውል በገባ/በገቡበት/ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን /ያሸነፉበትን/ ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርበታል/ ይኖርባቸዋል:: ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻለ ያስያዘ የጨረታ ማስከበሪያ ለኢ.ቅ.ባ ማሕበር ገቢ ይደረጋል::
- አሸናፊው ተጫራች በመንግሥት አዋጅ መሠረት የተጣለውን የሽያጭ ታክስ ሮያሊቲ ከፍያ በመንግሥት አሰራር መሠረት ለማሕበሩ የመክፈል ግዴታ አለበት።
- የቁም ዛፉን ቆርጦ ለማንሳት የተፈቀደው 9 (ዘጠና) ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል:
- ማሕበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቁ ነው፡፡
አድራሻ፦ በቦሌ መንገድ፣ ከቦሌ ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት ከሚገኘው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ ጀርባ፤ ከኢዮብ የድንኳን ሥራዎች እና የድግስ ዕቃዎች ማከራያ አጠገብ፣ በቀድሞው ራስ ከበደ መንገሻ ቤት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ጽ/ቤት
የቢሮ ስልክ ቁጥር – 01 15 15 88 02
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ