
Dessie City Water Supply and Sewerage Service Office
አዲስ ዘመን
(Dec 25, 2024)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ፓምፖች እና የመካኒካል እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እገልፃለን።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችል
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ማገኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)፤ በጥሬ ገንዘብ እና የባንክ ዋስትና (በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ 1 ኦሪጂናል እንዲሁም 1 ኮፒ በአጠቃላይ 2 ፖስታዎችን ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስገቡ እየገለጽን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን ነገር ግን 30ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- የቴክኒካልና ፋይናንሽያል ዶክመንት ለፓምፕና ሞተሮች ለማጫረት በተለያዩ ፖስታዎች ታሽጎ መቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ሲገለጽለት የውል ማስከበሪያ 10% ብር በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የባንክ ዋስትና (በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ ኣገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033-311-77-52፤ 092 020 8146 091 461 3590/098 988 7862 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት