
Nifas Silk Lafto Sub City Wereda 06 Administration FEDB
አዲስ ዘመን
(Nov 22, 2024)
የሐራጅ ጨረታማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ልማት ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ከደንብ ማስከበር የተወረሱ አልባሳት እና የቤት ቁሳቁሶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘው ለእያንዳንዱ ሰነድ በማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5/አምሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ምድር ላይ ቢሮ ቁጥር 1 የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 5000 (አምስት ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነዳቹ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ተጫራቾች የዋጋ መሙያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያ ከወጣበት አንስቶ ለ5 የስራ ቀናት ቄራ ጎፋ ገብርኤል 100 ሜትር ገባ ብሎ በወረዳው 06 አስተዳደር ደንብ ማስከበር ቢሮ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የንብረቶቹ ዝርዝር መመልከት ከተፈለገ በአስተዳደሩ ቅጥር ግቢ በደንብ ማስከበር ንብረት ክፍል ውስጥ መመልከት ይችላሉ።
- መነሻ ዋጋ በአንድ ላይ በጥቅል በመሙላት የሚወዳደሩ መሆኑን እያሳወቅን የመነሻ ዋጋ 129724.50 (አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሺ ሰባት መቶ ሀያ አራት ብር ከ50 ሳ)ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን ሰነዳቸው ላይ ማድረግ አለባቸው። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 6ኛው ቀን ጠዋቱ 3፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ላይ ይከፈታል።
አሸናፊ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን በተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ክፍያ በመፈጸም ንብረቶችን ማንሳት ይጠበቅበታል። ይህንን ሳያደርግ ቢቀር ያሲያዘው ሲፒኦ ተወርሶ ለቀጣይ አሸናፊ ይሰጣል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍስ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ልማት ጽ/ቤት