Kolfe Keranio Sub City Woreda 06 Health Post
አዲስ ዘመን
(Sep 13, 2024)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ቁጥር 001/2017 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ጤና ጣቢያ የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ ልዩ ልዩ የአገልግሎት ግዢዎች፤ ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችን እና የመኪና ጥገና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለእያንዳንዱ ሎት መያዝ ያለበት የጨረታ ማስከበሪያ ብር
- ሎት 1-መድሃኒት (20000.00) ብር
- ሎት 2-የጽህፈት መሳሪያዎች (16000.00) ብር
- ሎት 3-የደንብ ልብስ (11500.00) ብር
- ሎት 4-ለጽዳት እቃዎች (20280.00) ብር
- ሎት 5 ለቋሚ እቃዎች (38000.00) ብር
- ሎት 6-ለህትመት ስራዎች (15288.00) ብር
- ሎት 7-ለመኪና ጥገና (4950.00) ብር
- ሎት 8-ለልዩ ልዩ አገልግሎት ግዢ (6000.00) ብር
- ሎት 9 ለልዩ ልዩ የጥገና እቃዎች (11000.00) ብር
በመሆኑም
- በመንግስት እቃ አቅራቢነት ከመንግስት ግዢ ኤጀንሲ የምስክር ወረቀት ያለው፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ ቲን የምዝገባ ወረቀት ያላቸው ሆነው በዋጋ ዝርዝሩ ላይ ቫትን አካተው መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየሎቱ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከቢሮ ቁጥር 47 መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል ናሙና ለማቅረብ የማይመቹ እቃዎችን በፎቶ እና በካታሎግ ማቅረብ ወይም መስሪያ ቤቱ ድርጅቱ ድረስ ለሚልካቸው ኮሚቴዎች ተፈላጊ እቃዎችን ማሳየት ይኖርባቸዋል፡
- አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መሙላት አይቻልም፡፡
- ገዢው የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ድረስ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ እና ከላይ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በማስያዝ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
- አሸናፊዎች በሰነዱ ውስጥ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ያሸነፉበትን 10% ሲፒኦ በማሰራት ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ላይ በተቋሙ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች ኤክስ የሚያደርጉበት ቀን ቢያንስ ከአንድ አመት በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የእያንዳንዱ ሎት ኦሪጅናል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ መታሸግ ይኖርበታል፡፡
- መስሪያቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስቶር እስከማስገባት ድረስ ያለውን የማጓጓዣና የጉልበት ወጪ ተጫራቹ ይሸፍናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው በትክክል የተቋማችንን አድራሻ መግለጽ ይኖርበታል፡፡
- ከጥቃቅን እና አነስተኛ ጽ/ቤት የሚጻፉ ደብዳቤዎች በትክክል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ደብዳቤ መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል፡፡
- በሚጫረቱበት እቃ ላይ እሴት ለሚጨምሩ ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ልዩ ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- የጨረታው የስራ ቋንቋ የፌደራሉ የስራ ቋንቋ (አማርኛ) መሆን አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ቤተል ከአደባባዩ ዝቅ ብሎ ክፍለ ከተማው አጠገብ ወይም ፖስታ ቤት ፊት ለፊት፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118336993
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ጤና ጣቢያ