
Debre Markos Specialized Hospital
በኩር
(Nov 07, 2023)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2016 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
1. ለሆስፒታሉ ሠራተኞች ሰርቪስ የሚሰጥ 60 ሰው የሚይዝ ደረጃ 1 አውቶቡስ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፣
- የአገልግሎት መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሰክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የስ/ሂደት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ሲፒኦውን ጨምሮ ማንኛውም ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጣ ማንኛውንም ማስረጃ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/ አስ/ደ/የስ/ሂደት ክፍል ይካሄዳል።
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ።
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 2246 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአገልግሎት አይነቶች፡-
- ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰራተኞችን ከውሃ ጋኑ ሆስፒታል ድረስ፣
- ምሳ ሰዓት 6፡00ከውሃ ጋኑ አድርሶ መመለስ፣
- የመኪና ብልሽት ባጋጠመ ግዜ ተመሳሳይ መጠን የሚይዝ መኪና ማቅረብ የሚችሉ።
- የክፍያ ጊዜው የሚሆነው ወሩ በገባ 25ኛው እስከ 30ኛው ቀን ነው።
- አገልግሎት ባልሰጠበት ቀን ክፍያ አይፈፀምም።
የደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል