Mekane Hiwot Kindergarten and Primary school
አዲስ ዘመን
(Oct 06, 2023)
የጨረታ ማስታወቂያ
የመካነ ህይወት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በየሎቱ የሚመለስ የጨረታ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 6212 2000 ብር (ሁለት ሺህ ብር)፣
- አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች ሎት 6215 1000 ብር (አንድ ሺህ ብር)፣
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች ሎት 6218 3000 ብር (ሶስት ሺህ ብር)፣
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ ሎት 6211 2000 ብር (ሁለት ሺህ ብር)፣
- የህክምና እቃዎች
- ቋሚ እቃዎች ሲሆን ሎት 6313 እና 6314 500 ብር (አምስት መቶ ብር)፣
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመካነ ህይወት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚሆን ከላይ በየሎቱ የተጠቀሱትን ድምር ብር 8,500 / ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ወይም የሚወዳደሩበትን ሎት በመምረጥ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ሲኖርባቸው ያሸነፉበትን ገንዘብ 10% በቼከም ሆነ በጥሬ ብር ለዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻችው/ በተገኙበት ወይም ባይኖሩም በመካነ ህይወት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል።
- መሥሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ከ2 ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆን እንገልፃለን፡፡ ናሙና በማይቀርብባቸው እቃዎች ላይ በእስፔስፊኬሽናቸው መሰረት መቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ VAT ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን መሥሪያ ቤቱ የቀረበው ዋና VATን እንዳካተተ ይቆጥረዋል።
ለበለጠ መረጃ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ማዞሪያ አቦ ቤተክርስቲያን አጠገብ
ስልክ ቁጥር 011 114 0012 / 011 154 9341 ይደውሉ፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ት/ት ጽ/ቤት ወረዳ 2
የመካነ ሕይወት አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት