Ministry of Customs
አዲስ ዘመን
(Oct 06, 2023)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር:-01/ጋጥ/ገሚ/ዳ/2016
የገቢዎች ሚኒስቴር በ2016 በጀት ዓመት በባለቤትነት ለሚያስተዳድራቸው ከባድና አነስተኛ ተሽከርካሪዎች የጋራዥ ጥገና /የመለዋወጫ አቅርቦትን ያካተተ/ አገልግሎት ግዥን ለዓመታዊ ውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት:
- ሎት አንድ፡– ብዛታቸው ከአስራ አንድ /11/ በላይ ለሆኑ የቶዮታ መኪና ምርቶች በአይነት እስከ /አንድ መቶ ሰማንያ ሦስት/ 183/ የሚደርሱ የጥገና አገልግሎት ሥራዎች የመለዋወጫ አቅርቦትን ያካተተ ሥራ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00/
- ሎት ሁለት፡– ብዛታቸው ከአስራ ሦስት /13/ በላይ ለሆኑ የኒሳን መኪና ምርቶች በአይነት እስከ አንድ መቶ ሰማንያ ሦስት /183/ የሚደርሱ የጥገና አገልግሎት ሥራዎች /የመለዋወጫ አቅርቦትን ያካተተ ሥራ /የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00/
በዚሁ መሠረት ተጋባዥ ተጫራች ድርጅቶች፡–
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር ፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀትና የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ተጫራቾች በግዥ ኤጀንሲ ድረ–ገጽ ላይ የአቅራቢነት ፍቃድ የተመዘገባችሁበትን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባችሁ።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዱን በገቢዎች ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት ሕንፃ “መ” በቢሮ ቁጥር 301 ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት ከታች እስከተገለጸው የጨረታ መዝጊያ ዕለት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ ዝጅት፣ አቀራረብ፣ አመላለስ እና ሌሎች የጨረታ ማወዳደሪያ መስፈርቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተብራርተው ተቀምጠዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በገቢዎች ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት ሕንፃ “መ” በቢሮ ቁጥር 301 ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጥቀምት 13 ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊትና ልክ 4፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታ ቴክኒካል ዶክመንት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቦታና ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በገቢዎች ሚኒስቴር ስም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን ልክ ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች አሠርተው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ሕጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት።
- ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የገቢዎች ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት መገናኛ ወደ ሃያ አራት አካባቢ በሚያቋርጠው መንገድ አማካኝ ቦታ ላይ ሕንፃ መ ቢ.ቁ. 301
ተፈላጊ፡– አቶ ዳዊት ተስፋዬ ስልክ፡– 011 667 3845
የገቢዎች ሚኒስቴር