ብርሃን ቅድመ አንደኛ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብሶች ፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች ፣  የቢሮ ዕቃዎች  ፣ ህትመት ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ፣ የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Mezgebe Berhan Primary School

አዲስ ዘመን
(Sep 20, 2023)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ /ከተማ በወረዳ 2 ስር የሚገኘው የመዝገበ ብርሃን ቅድመ አንደኛ 1 እና መካከለኛ ደረጃ /ቤት 2016 የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ዥው መለያ ቁጥር 001/2016       
ሎት 1 የደንብ ልብሶች     የጨረታ ማስከበሪያ  የብር መጠን 7900 ብር
ሎት 2 አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችና የቢሮ ዕቃዎች   4300 ብር
ሎት 3 ህትመት    2000  ብር
ሎት 4 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች   1800 ብር
ሎት 5 የፅዳት ዕቃዎች    8200 ብር
ሎት 6 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች  1000 ብር
ሎት 7 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
4200 ብር
ሎት 8 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
2500 ብር
ሎት 9 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
1000 ብር

 በዚህ መሠረት በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ፡

 • የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ የዘመኑን ግብር አጠናቃችሁ የከፈላችሁ በመንግሥት //አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ የቫትና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።
 • የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ በተረጋገጠ ቼክ / CPO/ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ የምትችሉ።
 • የጨረታ አሸናፊ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
 • ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ሰነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመዝገበ ብርሃን ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
 • ተጫራቾች የምትጫረቱትን ዕቃ ሎት 1 ፣ ለሎት 2 ፣ ለሎት 3 ፣ ለሎት 4 ፣ ለሎት 5 ፣ ሎት 6 ፣ ሎት 7 እና ሎት 8 ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባችሁ።
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
 • የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
 • አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሱ /ባሸናፊው/ ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው /ቤት ድረስ ማቅረብ ግዴታ አለበት።
 • ተጫራቾች የምታቀርቡትን ዋጋ ዝርዝር በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልታችሁ በሰም በታሸı ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በሥራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን በመዝገበ ብርሃን ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት ማስገባት ይኖርባችኋል።
 • የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት 10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል። 10ኛው ቀን የበዓል ቀን ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
 • መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ጦር ኃይሎች የቀድሞው ኦሜድላ ጀርባ በተለምዶ አይነስውራን ድርጅት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፡-011-371-0357 /011-369-0534

በልደታ /ከተማ አስተዳደር ትምህርት /ቤት

መዝ ብርሃን የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት