Dire Dawa Adminstration Women, Children and Youth Affair Bureau

መልዕክተ ድሬ
(Sep 13, 2023)

ማስታወቂያ

1. የሞተር ሳይክል ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 004/2016

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው 180 ሲሲ ሀፓች ሞተር ሳይክል ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) በመክፈል ከድሬዳዋ ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ግዥ ክፍል ቁጥር 4 በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ የያዘውን ሰነድ በሰም በታሸገ  ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት በኃላ (16ኛው የስራ ቀን) ከጠዋቱ 330 ድረስ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀውና በግዥ ፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ፡

  • የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ (ቢድ ቦንድ) በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • አንድ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር አይችልም።
  • በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስመስከሪያ ገንዘብ ወድያውኑ የሚመለስላቸው ሲሆን የአሸናፊዎች ግን ከመ/ቤቱ ጋር ውል ሲፈፅሙና የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲያሲዙ ብቻ የሚመለስ ይሆናል።
  • የጨረታው አሸናፊዎች 15 ቀን ጊዜ ውስጥ ቀርበው ውል ባይፈፅሙና የውል ማስከበሪያ ባያሲዙ የጨረታ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ የሚወረስ ይሆናል።
  • የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጨምሮ 15 ቀናት በኋላ (በ16ኛው የስራ ቀን) ከጠዋቱ 330 ይታሸጋል።
  • ጨረታው 16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
  • /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥሮች 025 113 0809/ 025 111 3634 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ