Sheger City High Court, Sululta District Court
አዲስ ዘመን
(Sep 11, 2023)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ፍ/ቤት በ2016 ዓ.ም በስሩ ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች
- የሚያገለግል ቋሚና አላቂ እቃዎችን ፣
- የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ እና TIN ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ለዚሁም የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች መካፈል ይችላሉ፡፡
- ለአነስተኛ እና ጥቃቅን የግብር ከፋይ ክሊራንስ እና የ2015ዓ.ም ኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት እቃ ናሙና (sample) ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከሱሉልታ ክፍለ ከተማ ፍ/ቤት ዕቃ ግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ21ኛው የሥራ ቀን በ4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በ21ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታ ሰነዱ እስከ 4፡00 ገብቶ ወዲያው 4:30 የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ይመለሳል።
- ለጨረታው የሚቀርበ ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች ዋጋ ማቅረቢያ ሲያቀርቡ ሁሉንም እቃዎችን ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታዉ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሰው ዋጋ የጨረታው ሂደት አልቆ ርክክብ እስከሚደረግ ድረስ ዋጋው የፀና ይሆናል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊዎች የአሸነፍበትን እቃዎች በጠቅላለ በራሳቸው ትራንስፖርት አምጥተዉ ዕቃ ግምጃ ቤት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እየገለጽን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0921 80 18 13/0909 14 99 05 / በመደወል ወይም ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ፍ/ቤት ዕቃ ግዥ ክፍል በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ፡፡
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ፍ/ቤት