Ethiopian Revenue and Custom Commission Modjo Customs Branch Office
አዲስ ዘመን
(Sep 04, 2023)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 51፤ ንዑስ አንቀፅ 1 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ 1160/2o11 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ዕቃዎችን የጉምሩክ ሥነሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተዉ ተቆጥረዋል። ስለሆነም በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጉምሩh ቁጥጥር ሥር ያሉ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት ባወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም BABY FEEDING BOTTLE 150 ML AND 250 ML
- (የህፃናት ጡጦ ጠርሙስ)፣
- SODIUM LAURYL ETHER SULPHATE 70% (ኬሚካል)፣
- ከፕላስቲክ የተሰሩ የተለያዩ መጠን ያላቸው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣
- GARDEN UMBRELLA፣ ድንኳን እና TEMPERED GLASS TABLE
- (የቡና ጠረጴዛ)፣ WHITE PLAIN PAPER 51,850 KG፣ SNOW RABBIT C2S ART PAPER SIZE=60*860MM 63,207 KG (ወረቀት) ፣
- ጀኔሬተር እና IRON OXIDE RED 10 (ኬሚካል) ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት እና ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT፣ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውም ዕቃ ለመግዛት የ5% የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው አንዲታወቅ በ3 ሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ካሸነፉበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን የግል ባንh ከሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርንጫፍ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፍ ማዘጋጀት አለበት። ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅተው ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወሰድም።
- የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች ዕቃዎችን ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ የሞሉበት ሠነድ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ጠዋት 4፡45 ሰዓት ድረስ በቅርንጫፍ ጽ ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
- የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- የጨረታ ማስታወቂያው የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም።
- ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጨረታውን ለማሸነፍ ሲል መደለያ የሰጠ ወይም ለስጠት የሞከረ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ይወዳል። ጨረታው ከተካሄደ በኋላም ቢሆን የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈው በህገ ወጥ መንገድ መሆኑ ከተረጋገጠ የጨረታውን ውጤት ይሰረዛል።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- የግልፅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሰት ገቢ ይደረጋል። ያሸነፉት ዕቃም በድጋሚ ለጨረታ ሽያጭ ይቀርባል።
- በተራ ቁጥር 12 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተዉ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳሉ።
- አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለጨረታ ያቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር፡– 022-236_90_94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት