
Customs Commission Jigijiga Branch
አዲስ ዘመን
(Sep 01, 2023)
የግልጽ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ከ26/12/2015 ዓ.ም ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለጹትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልጻል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
- ለሐራጅ ጨረታው ለእያንዳንዱ መኪና 100,00 (አንድ መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ የሚችል፤
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተሽከርካሪውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቹ ለሐራጅ ጨረታ ለእያንዳንዱ መኪና የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል።
- ለግልጽ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን መኪና ወዲያውኑ ከፍሎ በ5 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት።
- መኪናውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ5 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲፒኦ (CPO) ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ሲፒኦ (CPO) አሠርቶ ማምጣት አለበት።
- አሳማኝ የሆነ ምከንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች መኪናውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
- ተጫራቹ መኪናውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
- ተጫራቾቹ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ በ2/13/2015 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 3፡45 ሰዓት በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ማስገቢያ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በ2/13/2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚከፈት ይሆናል።
- የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው በ2/13/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ 15% /አስራ አምስት ፐርሰንት/ የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት