Gendekore Health Offce

አዲስ ዘመን
(Aug 29, 2023)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የገንደቆሬ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዢዎችን ለመፈፀም አቅራቢ ድረጅቶች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  • 1ኛ ሎት አንድ የቢሮ የፅ/መሳሪያ፣
  • 2ኛ ሎት ሁለት የተለያዩ የፅዳት እቃዎች፣
  • 3ኛ ሎት ሶስት መድሃኒት ሪኤጀንት፣
  • 4ኛ ሎት አራት ህትመት፣
  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. በመንግስት ግዢ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በገንደቆሬ ጤና ጣቢያ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ድ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራች ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼከ ወይም /CPO/ ወይም (BID BOND) ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኃላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 2፡30 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
  8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጤና ጣቢያው ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማስረጃ፡- 025-113-0761 ሞ/ል 0911-81-51-59 እና 0924-12-45-10 መደወል ይቻላል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የገንደቆሬ ጤና ጣቢያ