Ethiopian Revenue and Custom Commission Bahir Dar Branch Bureau

አዲስ ዘመን Sep 23, 2022

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 03-2015

በኢትዮጵያ ጉምሩ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ

 • የተለያዩ ተሸከርካሪዎች ፣
 • የተለያዩ አልባሳት ፣
 • ሽቶ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፣
 • ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌከትሪክ ዕቃዎች መለዋወጫዎች
 • የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችንና ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ እና በሀራጀ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን
 1.  በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር . ያ በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ
  እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ
  መ/ቤት የሚሰጥ – ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር
  ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 2. በተሸከርካሪዎች ጨረታ ዕድሜው ከ18 ዓት በላይ የሆነ ከተሽከርካሪው አስጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሌሎች በተቁ 1 የተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ (መታወቂያ) ኮፒ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
 3. ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500ሺ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች 5 ( የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሁኖ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም/ ያስፈልግም።
 4. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች እስከ መስከረም 20/2015 ዓ.ም ድረስ ለሀራጅ ጨረታ የቀረቡትን ደግሞ እስከ መስከረም 21/2015 ዓም 5፡00 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት  ይችላሉ።
 5. ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 18 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 20/2015 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ 2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 መግዛት ይችላሉ።
 6. የግልፅ ጨረታው መስከረም 21/2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 2፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል።
 7. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) (ኢትዮጵያ ጉምሩh ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ መስከረም 21/2015 ዓም ከጠዋቱ 2፡45 ድረስ ቢሮ ቁጥር 502 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
 8. በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያልያሳዘ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
 9. የሀራጅ ጨረታው መስከረም 21/2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 5፡30 ጀምሮ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል።
 10. ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተማሪ እሴት ታክስ /ቫት (5%) የሚጨር ይሆናል።
 11. ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚለስላቸው ይሆናል።
 12. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ በአምስት ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
 13. ከላይ በተ/ቁ 12 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕ>ው በድጋሜ ለጨረታ ይቀርባል።
 14. በጨረታ ከሚሽጡ ተሸከርካሪ ስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል ማንኛውም ወጭ መ/ቤቱ አይሽፍንም።
 15. በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም።
 16. ለግልፅ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
 17. በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃውን አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
 18. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙለ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት እና ለሃራጅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር ከተቋሙ ማስታወቂያ ቦርድ በመመልከት እና በስልh ቁጥር 058-320-7418 / 058-320-7569 በመደወል ተጨማሪ ረጃ ማግኘት የምትችሉ ሆኑን እንገልፃለን። አድራሻ፤- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራhሽን ድርጅት ቢሮ ጎን

በኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት