Kombolcha Animal Disease Diagnostic Research Laboratory

በኩር Sep 19, 2022

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚዉሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች/አገልግሎቶች/ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል።

 •  ሎት 1 የመኪና ጥገና ጋራዥ ለመደበኛ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ
 •  ሎት 2 የመኪና ጥገና ጋራዥ ለፕሮጀክት ለ2ኛ ጊዜ የወጣ
 • ሎት  3 የመኪና እቃ መደበኛ
 • ሎት 4 የመኪና እቃ ፕሮጀክት

በግልፅ ጨረታ /በሎት ሲስተም/ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል።

 1. በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ።
 2. የቫት /እሴት ታክስ /ተመዝጋቢ የሆኑ።
 3. በአዲሱ የንግድ ፈቃድ መሠረት ንግድ ፈቃድ ያወጡ።
 4.  የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
 5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / የቲን ተመዝጋቢነት ሠርትፊኬት ያላቸዉ።
 6.  የመኪና ጠገና አሸናፊ ከሆኑ በአሸነፉበት ዋጋ ለአንድ አመት ዉለታ ገብተዉ አገልግሎቱን ሊሰጡ የሚችሉ።
 7.  ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
 8.  የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማገኘት ይችላሉ።
 9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ ሠነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል ለኮ/እ/በ/ቅ/ጥ/ም/ላብራቶሪ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ።
 10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃ አጠቃላይ ዋጋ 3 በመቶ አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ።
 11. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለኮ/እ/በ/ቅ/ጥ/ም/ላብራቶሪ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሠአት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 12. ጨረታዉን ካሸነፉ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸዉ።
 13. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በኮ/እ/በ/ቅ/ጥ/ም/ላብራቶሪ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ከ9/1/15 እስከ 23/01/2015 ዓ/ም ቀን ጀምሮ ተቆጥሮ በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ተዘግቶ በዚያዉ ቀን 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን የተጠቀሰዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን በዚያዉ ሠአት ይከፈታል።
 14. የመኪና ጥገና ተጫራቾች ደረጃ 3 እና በላይ ያላቸዉ መሆን አለባቸው።
 15. መልካም ስራ አፈፃጸም ማቅረብ የሚችሉና ኢንሹራንስ ያላቸዉ መሆን አለባቸው።
 16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
 17. በጨረታዉ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 351 8843 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ