Yeka Sub City Woreda 10 Health Post

አዲስ ዘመን Sep 18, 2022

የጨረታ መለያ ቁጥር የካ/ወ/10/ጤ/ጣ/001/2015

በየካ ክ ከተማ አስ/ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው ፋይናንስ ክፍል በኘት ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ በሎት ብር 50/ሃምሳ ብር ብቻ/በመፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ሳወቅን በሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ በማቅረብ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን 03፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 3፡30 ላይ ነጋዴዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቾ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

 1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ
 2. የህከምና መገልገያ ዕቃዎች እና መድሃኒቶች ግዥ
 3. የጽዳት ዕቃዎች ግዥ
 4. ደንብ ልብስ ግዥ
 5. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ
 6. ህትመቶች
 7. ፎቶ ኮፒ ማሽን፤ ኮምፒዩተር ላፕቶፖች ፕሪንተሮች የመሳሰሉትን ጥገና
 8. የደንብ ልብስ ስፌቶች
 9. የቋሚ ዕቃዎች ግዥ

ማሳሰቢያ፡እያንዳንዱ ነጋዴ |ተጫራቾች|

 1. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጤና ጣቢው ስም የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ለእንዳንዱ አልግሎት በሲፒኦ 2000.00/ ሁለት ሺ ብር ብቻ| ለጤና ጣቢያው ፋይናንስ ማስረከብ አለበት
 2. ደንብ ልብስ ግዥ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ፣ ለፅዳት እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ያላቀረበ ድርጅት በጨረታው አይካፈልም።
 3. የህከምና መገልገያ ህትመቶች ናሙና ጤና ጣቢያው በሚያቀርበው ናሙና መሰረት የሚሰራ ይሆናል።
 4. የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ ቫትን ያላካተተ ድርጅት በጨረታው አይተፍም
 5. .የኮምፒውተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ቀለም የአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
 6. .ለ2015 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ፣እና የእቃ አቅራቢነት የምስር ወረቀት ያለው።
 7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
 8. የደንብ ልብስ ስፌቶችን በተመለከተ ተሰፍቶ እስኪያልቅ ድረስ ጤና ጣቢያው ግቢ ውስጥ በሚያጋጀው የመስሪያ ቦታ ሰርቶ የጊዜ ገደቡ እስከሚያልቅ ድረስ ተቀምጦ ማስረከብ የሚችል።
 9. ፎቶ ኮፒ ማሽን፤ ኮምፒዩተር ላፕቶፖች ፕሪንተሮች የመሳሰሉትን ዋጋ ሲሞላ ለጥና የሚያስፈጋቸውን ግበዓት (የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች) አንድ ላይ ተደርጎ መሞላት አለበት።

አድራሻ፡- ኮተቤ 02 ወደ ህዝብ ደህንነት በሚወስደው መንገድ ወደ ላይ ወጣ ብሎ ከወረዳ 10 አስተዳደር ፊት ለፊት ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር/011 825 5495/011 860 3710

የካ ክ/ከተማ አስ/ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 10 ጤና ጣቢያ