
Arba Minch Poly Technic & Satellite Institute
አዲስ ዘመን Aug 06, 2022
የጨረታ ማስታወቂያ
በ/ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ትምህርት ሥልጠና ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ ሥራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟላ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት
- ደረጃቸው GC-5/ BC-5 እና ከዚህ በላይ የሆነ
- ፈቃዳቸውንና የምዝገባ ሰርተፍኬታቸውን ለ2014 ዓ.ም. ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት ከኮሌጁ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የሥ/ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች 500,000( አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰንድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና ጠቅላላውን ሠነድ በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 -6:00 ሰአት ኮሌጁ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት አለባቸው ።
- ጨረታው በ31ኛው ቀን ከቀኑ ከ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ኮሌጁ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እያሳወቅን የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 እና በመመሪያው ላይ የተደረገውን ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሰርኩላር ተፈፃሚ ያደርጋል።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፦046 881 3659
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት
አርባ ምንጭ