
Guto Gida Woreda Revenue Authority District Office
አዲስ ዘመን Aug 06, 2022
ለ1ኛ ጊዜ በዕዳ የተያዘ ንብረት
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
በአሮሚያ ገቢዎች ቢሮ የምስራቅ ወለጋ ዞን የጉቶ ግዳ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የክልሉ ግብር/ታክስ ከፋይ የሆነው ተወልደ ገ/ሥላሴ ወይም ባለቤቱ ወ/ሮ ነብያት ግደይ የሚፈለግባቸውን የመንግስት ታክስ/ግብር ባለመክፈላቸው በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 203/2009 ዓ.ም. አንቀፅ 43 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ያልተከፈለውን የመንግስት ታክስ/ግብር ለማስከፈል የታክስ ባለዕዳው ንብረት የሆነውን ቤት ተይዞ ባሉበት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ወለጋ ዞን በጉቶ ጊዳ ወረዳ ኡኬ ቀበሌ 01 ያለውን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም:
- ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው በጨረታው ለመሳተፍ የሚችል ሲሆን የንብረቱን መረጃ የሚያመላክት የጨረታ ሰነድ እና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በአሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ምስራቅ ወለጋ ዞን የጉቶ ግዳ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቹ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አሥር) ቀናት ለሽያጭ የተዘጋጀውን ቤት በሚገኙበት ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስ/ወለጋ ዞን ጉቶ ጊዳ ወረዳ ኡኬ ቀበሌ 01 በሚገኘው በምስራቅ ጃሚላ ሞሃመድ ፣ በምዕራብ ቶላሳ ሶር በሰሜን ጌቱ ደሱ በደቡብ መንገድ በሚያዋስነው ቤት ካርታና ፕላን ቁጥሩ የሆነውን ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቹ ቤቱን ለመሸጥ የተቀመጠውን መነሻ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የክፍያ ማስያዣ ሲ.ፒ.ኦ ( C.P.O.) ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቹ የቤቱን መረጃ በያዘው ላይ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በአምድ (column) ሥር ቤቱን የሚገዛበትን ዋጋ በአኃዝ እና በፊደል ለይቶ በትክክል ጽፎ ከፈረሙ በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጎ ለጨረታው በተዘገጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቹ አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ያሸነፈበትን የቤቱን ዋጋ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከፍለው ቤቱን የመረከብ ግዴታ አለበት።
- ከስም መዘዋወር ጋር የተያያዙ ወጭዎች በአሸናፊው ተጫራች ይሸፈናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በጉቶ ጊዳ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ጊቢ ውስጥ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 10፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ይከፈታል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ ሥልክ ቁጥር 0913 07 03 96 ወይም 0917 85 34 07 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ምስራቅ ወለጋ ዞን ገቢዎች ጽ/ቤት የጉቶ ግዳ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት