• Sidama

Customs Commission Hawassa

አዲስ ዘመን Aug 06, 2022

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ //ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2015

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ //ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን // ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ የመገናኛ መሣሪዎች

 • የንጽህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች
 • የመኪና መለዋወጫዎች
 • የትራክተር መለዋወጫዎች
 • የቤትና የቢሮ ዕቃዎች መገልገያዎች እና
 • ያገለገለ ሞተር ሳይሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

 1. ተሽከርካሪዎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መወዳደር ይችላል።
 2. ግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ የምስ ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
 3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2:00 እስከ 6:00 ከሰዓት 7፡00 እስከ 1100 ሰዓት ቅዳሜ 200 እስከ-6oo ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ) በመክፈል በቅ//ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
 4. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበት ጠቅላለ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) (ኢትዮጵያ ንግድ ባን የተመሰከረለትን C.P.O የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ማንኛውም የሃራጅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ለትራክተር መለዋወጫ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለሞተር ሣይክል ለእያንዳንዱ ኮድ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እና የንፅህና መጠበቂያ ብር 30,000(ሰላሳ ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰክረለትን C.P.O ማቅረብ ይኖርበታል።
 5. ይህ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6ኛው (ስድስተኛው) ቀን የግልፅ ጨረታ ጠዋት 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 405 የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታ 430 በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ይጀመራል ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድ/ቀን ሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የስራ ቀናት ይሆናል።
 6. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ከፍት ቦታ ከነ ቫት እና ያለቫት በሚል በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ //ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
 7. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።
 8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ //ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
 9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
 10. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
 11. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ባለሥልጣኑ ተጠያቂ አይሆንም።
 12. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
 13. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5(አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስበሪያ ዋስትና ለቅ//ቤቱ ገቢ ይሆናል።
 14. //ቤቱ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ር፡-046 212 5396

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት