
Tis Esat Water Works PLC
አዲስ ዘመን (May 14, 2022)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
ተ.ቁ
|
ሎት
|
የዕቃው አይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
1 |
ሎት1 |
ፓምፕና ጄኔሬተር |
100,000.00 |
2 |
ሎት2 |
የኤሌክትሪክ ገመድና ሌሎች ተያያዥ ዕቃዎች |
50,000.00 |
3 |
ሎት3 |
የግንባታ መገልገያ መሳሪያዎች |
50,000.00 |
4 |
ሎት4 |
የመጠጥ ውሃ ስካዳ ሲስተም (SCADA system) አቅርቦትና ተከላ ስራ |
200,000.00 |
5 |
ሎት5 |
አፍሬዲቭ ፓምፕ (afrediv pump) |
30,000.00 |
6 |
ሎት6 |
ስቲል ኬዚንግ (steel casing) |
50,000.00 |
7 |
ሎት7 |
ለቁፋሮ የሚውል ፎም (drilling foam) |
30,000.00 |
8 |
ሎት8 |
ጎማ |
30,000.00 |
9 |
ሎት9 |
ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ |
100,000.00 |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን ኩባንያችን ጽ/ቤት ማግኘት ይችላል።
የተጫራቾች መመሪያ፣
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድረ–ገጽ www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱ ዕቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR-02/2013 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
- ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (an unconditional Bank Guarantee) ለማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው መሰረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡– ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ሳይሆን በእያንዳንዷ ዕቃ ነጠላ ዋጋ በሚሞሉት ዋጋ መሰረት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26 /058 3202 548/
በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 ይጠቀሙ።
የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር