
Akaki Kaliti Sub City Woreda 6 Administration F/E/D/B
አዲስ ዘመን (May 14, 2022)
የጨረታ ማስታወቂያ ሽያጭ
መለያ ቁጥር 02/14
የአቃ/ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት በጎደና ላይ በሕገ ወጥ ነጋዴዎች የተወረሱ የተለያዩ አልባሳት እና መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ማለትም፡
ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች :
- የተለያዩ የሕፃናት እና የአዋቂ አልባሳት እና ጫማዎች
- የተለያዩ የቤት ዕቃዎች
- የአሻንጉሊት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተወዳዳሪዎች ለውድድር ያመቸው ዘንድ ዕቃዎች ያሉበት ሁኔታ አይቶ ለመወሰን ለ7 ተከታታይ የስራ ቀን ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመሸጥ በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 1% ብር በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በሚል ስም አሰርቶ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቶች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፣
- ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የለባቸውም፣
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት
ሳሪስ ንብ ባንክ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0118889529 ስልክ 0118889512
በአቃ/ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት