
Amhara National Regional State Education Bureau
አዲስ ዘመን (May 14, 2022)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EB/EMAS/07/2014
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ (GEOP-E በጀት ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ
- ቴሌቪዥን ፣
- ዲጂታል ፎቶ ካሜራ ፣
- ሄድፎን ፣
- ዲጂታል ሪኮርደር ፣
- ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች ፣ ሸልፎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በህጋዊ የታደሰ ህጋዊና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ፤
- የሚቀርቡ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 103 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 10.1 የተመለከተውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ ከቢሮው የሚሰጣቸውን የገቢ ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ግብዓት ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋዉ በዓል ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582201100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583295654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
ባህር ዳር