fbpx
 • Wollo

Customs Commission Kombolcha Branch Office

አዲስ ዘመን (May 14, 2022)

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 13/2014

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዬ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ኮስሞቲክስ በግልፅ ጨረታ ተሽከርካሪዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ እንፈልጋለን።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ

 1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ አለበት። ለተሽከርካሪዎች ማንኛውም 18 አመት በላይ የሆነው መጫረት ይችላል።
 2. በተጠቀሰው መስፈርት በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
 3. የጨረታ ሰነድና መመሪያ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ለመግዛት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
 4.  የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው ሊሳተፍ አይችልም። እንዲሁም በኮፒ የጨረታ ሰነድ መጠቀም አይችልም።
 5. ተጫራቾች ለኮስሞቲክስ ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለተሽከርካሪ 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊ ለሆኑት የጨረታ ማስከበሪያው በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ የሚታሰብ ይሆናል። ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ያስያዙት ቼክ (CPO) ተመላሽ ይሆናል።
 6. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር ስያዘው ሰነድ ላይ በየእቃ አይነቶች (ኮድ) ተጫራቹ መጨረሻ (ግርጌ) ላይ የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ዕቃዎች የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋን በመንተራስ ነው። ለተሽከርካሪዎች መርጠው መጫረት ይችላሉ። የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ ተጫራቹ መፈረም አለበት።
 8. ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ሳይጨምር ሆኖ ነገር ግን የጨረታው አሸናፊ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) 15% ተጨማሪ እንደሚሆን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
 9. ከጨረታ መዝጊያው ሰአት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም። ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (እቃው በሚገኝበት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ቢሮ) ይሆናል።
 10. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሁኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
 11. ሁለት ተጫራቾች ለአንድ እቃ እኩል ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ቢሆኑ እንደገና በማወዳደር አሸናፊው እንዲለይ ይደረጋል።
 12. . ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር አይነትና ብዛት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት 10፡00 ሰዓት ድረስ ማየት የሚቻል ሲሆን ጨረታው የሚከናወነው በስምንተኛው ቀን 3፡45 ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን የሃራጅ ጨረታው 5፡00 ሰአት ይጀመራል። ተጫራቶች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ መውጣት አይችሉም። ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ውጤት እስከሚገለፅ ድረስ ጸንቶ ይቆያል።
 13. . ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመከፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።
 14. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 15. የሰነድ መግዣ ቦታ በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ ሂሳብ ቡድን ቢሮ ቁጥር 103 ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-033 551 0693 ደውሱ መጠየቅ ይቻላል።

የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት