
Amhara National Regional State Agriculture Bureau
አዲስ ዘመን (May 14, 2022)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ በመደበኛ የግዥ ህግ መሰረት በ2014 ዓ/ም በጀት አመት በተፈቀደለት መደበኛ በጀት
- የኤሌክትሮኒከስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 በላይ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቨት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ከአርጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 100 ገዝቶ በመውሰድ ቢሮ ቁጥር 12 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት አቅርቦት ለሚሞሉት ብር 100000.00/አንድ መቶ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያዉ ቅጽ መሰረት የአንዱን የነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ ፋይናንሻል ሰነድ በማሸግ በፖስታማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አብክመ ግብርና ቢሮ ግዥ ክፍል /ቢሮ ቁጥር 12/ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታዉ ማስታዎቂያ ከወጣበት ጀምር ለ5ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡ ቀኑ በዓል/ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆኑ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- ቢሮው የተሻለ አራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስቁጥር 0582265521 በመላክ ወይም ስልክቁጥር 0582266431 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
ባህር ዳር