
Sidama National Regional State Office of Women, Youth and Social Affairs
አዲስ ዘመን (May 14, 2022)
የጨረታ ማስታወቂያ ኮድ 003
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2014 በጀት ዓመት በሀዋሳ ከተማ በታቦር ክ/ከተማ ጥልቴ ቀበሌ ሊያሠራ ያቀደውን የሞዴል ወጣቶች ማዕከል
- የአጥር ጥገና ሥራ ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት :
- ደረጃቸው GC-7/BC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች በ2014 ዓ/ም የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው መንግሥት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ እና አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- አስፈላጊውን የግንባታ ዕቃዎች፣ የሥራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው::
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መሥሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
- ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋናው ውል ስምምነት ገብተው ሦስትና ከዚያ በላይ ሥራ ጀምረው ያላጠናቀቁ (ያልጨረሱ) ተቋራጮች ጨረታውን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
- የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት(ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው ፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳከሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው (bid security) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፡
- የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ /VAT/ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ14 (አሥራ አራት ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሴቶች ፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ግዥ/ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ::
- የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታን ቦታ በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያው (bid security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከመጣበት ቀን አንስቶ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሴቶች ፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ግዥ/ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያዉ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር.9 ላይ በተገለፀው ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሠዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- የአሠሪ መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-0912187977/0916824243
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ሀዋሳ